Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 316 የሱስ አዳኜ ምራኝ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 316 የሱስ አዳኜ ምራኝ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ የሱስ አዳኜ ምራኝ
አስበኝ በባሕር ላይ።
ማዕበልም ቢገጥመኝ
የተሰወረም ድንጋይ።
እንዳልጠፋ አስበኝ
የሱስ አዳኜ ምራኝ።
፪፡ ልጅ ላባቱ ዝም እንዲል
እንዲሁ ታላቅ ሞገድ።
ለቃልህ ይታዘዛል
ስትለው ጸጥ በል ታገድ።
በባሕርም ላይ አዳኝ
የሱስ አዳኜ ምራኝ።
፫፡ ከባሕሩ ዳር ስደርስ
ለመሻገር ተጕዤ
ሞገዱ ሲተራመስ
በክንድህ ተመርኩዤ
ጌታ ልስማ ስትለኝ
አትፍራ ካንተ ጋር ነኝ።

Exit mobile version