መዝሙር 310 ይመራኛል ይመራኛል የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ይመራኛል ይመራኛል
እንዴት ያለ መጽናናት ነው።
በሄድሁበት ባለሁበት
ይጠብቀኛል በሕይወት።
ይመራኛል ይመራኛል
ጌታ የሱስ ይመራኛል
በመንፈሱ ከተመራሁ፥
ተከታዩ እሆናለሁ።
፪፡ ጌታዬ ሆይ እኔን እርዳኝ
ከማጉረምረምም ጠብቀኝ።
በፈተና ኃይል እንዳገኝ፥
አምላኬ ሆይ እኔን እርዳኝ።
ይመራኛል . . .።
፫፡ በዚህ ዓለም ስትመራኝ
በጸጋህ ካገኘሁ ሁሉን።
አልፈራም የሞትን ጥላ፥
አንተ ካለህ ከኔ ጋራ።
ይመራኛል . . .።