Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 309 ጌታ ሞገዱ በረታ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 309 ጌታ ሞገዱ በረታ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ጌታ ሞገዱ በረታ
ማዕበሉም ተናወጸ፥
ሰማይና ምድር ጨለመ፥
የመዳን ተስፋ ራቀን።
አይገድህም ወይ ስንጠፋ፥
ለምን ዝም ትላለህ፥
በሁሉ ነገር ተስፋ ቆረጥነ፥
ለመስጠም ተቃረብነ።
ባሕር ነፋስ ይታዘዙታል ሲል ጸጥ በል
ማዕበል ቢናወጥ ሞገድም ቢያይል፥
የመጣ ቢመጣ የሆነ ቢሆን።
የጌታን ሰላም ከቶ አያጠፋውም፥
ከሃሊው ጌታ አይለየንም።
ሁሉም ለቃሉ ይታዘዛል
ሲል ጸጥ በል ሲል ጸጥ በል፥
ሁሉም ለቃሉ ይታዘዛል ሲል ሰላም ይሁን።
፪፡ ጌታ ሆይ፥ በጭንቀት መንፈስ
በፊትህ ተንበርከኬ
የፍርሃት ሞገድ ሲያጉላላኝ
ንቃ ስማ ጸሎቴን።
የኃጢአት ክብደት ተጭኖኝ፥
ነፍሴን ሊያወድም፥
መጥፋቴ ነው መጥፋቴ ነው ጌታ፣
አድነኝ አንዳልሰጥም።
ባሕር ነፋስ . . .።
፫፡ ጌታ ሆይ፥ ሞገዱ አለፈ
ሁሉም ነገር ጸጥ አለ።
የሰላምም መንፈስ ሰፈነ፥
ምድሪቱንም ሸፈነ።
ከኔ ጋር ሁሉ አትለየኝ፥
ታማኙ መድኅኔ።
ላመስግንህ ባሕሩን ተሻግሬ፥
በወደቡ ዳር ቁሜ።
ባሕር ነፋስ . . .።

Exit mobile version