Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 299 አምላክ ሆይ አንተ ጠብቀኝ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 299 አምላክ ሆይ አንተ ጠብቀኝ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ አምላክ ሆይ አንተ ጠብቀኝ
በቀናው መንገድህም ምራኝ
ጨለማውን መንገድ አብራልኝ
ሕግህን እንድጠብቀው።
ኃጢአቴ ይሰማኛል
ሸክሙም በጣም ይከብደኛል።
በደሌን ደምስሰህ አንጻኝ
አምላኬ ሆይ ይቅር በለኝ።
፪፡ ቸር ጌታ ሆይ አትተወኝ
አንተ ራስህም ጠብቀኝ፡
ታላቅ ፍቅርህ አይለየኝ
ልመናዬን ስማልኝ።
በሰማይና በምድር
ሁሉን ቻይ አምላክ አንተ ነህ
በመንፈስ ቅዱስ አበርታኝ
ኃጢአቴን ደምስስልኝ።
፫፡ እንዳልካቸው ሐዋርያትን
ሂዱና ቃሌን አስተምሩ
መጣሁ ለመስማት ቃልህን
አእምሮዬን ክፈትልኝ።
ልቤን አንጽተህ ኑርበት
ጠላቴ እንዲርቅልኝ
ከክፉ ሁሉ አድነኝ
ጸሎቴን ስማልኝ አሜን።

Exit mobile version