መዝሙር 296 የሱስ አምላኬ ሆይ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የሱስ አምላኬ ሆይ
ለቃልህ ታዝዤ
ወዳንተ እቀርባለሁ፤
ጸጋህንም እሻለሁ።
በደምህ ከኃጢአቴ
ይነጻል ሕሊናዬ።
፪፡ ዘላለም ያንተ ነኝ
በጸጋህ ጠብቀኝ
ከአንተም ከሚለየኝ
እንድርቅ ረድኤት ሁነኝ።
ሞት ከቶ በማይደረስብኝ፤
በመንግሥትህ አኑረኝ።