መዝሙር 289 መንግሥቱ ለዘላለም የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ መንግሥቱ ለዘላለም
መንግሥቱ ለዘላለም
ምሕረቱ ብዙ ነው
ፍቅሩም ለልጅ ልጅ ነው።(4)
፪፡ አክብሩት አምላካችንን
አምልኩ እግዚአብሔርን
የእጆቹን ሥራ
ቸል አላለምና።(4)
፫፡ አውጁ ቃሉን መስክሩ
አውጁ ቃሉን መስክሩ
ቅዱስ አማኑኤል
ከኛ ጋር ነውና(4)
፬፡ ዘምሩ ስሙን ወድሱ
ዘምሩ ስሙን ወድሱ
በዕልልታ ጸናጽል
ጌታን አመስግኑ።(4)
፭፡ መንግሥቱ ለዘላለም
መንግሥቱ ለዘላለም
ምሕረቱ ብዙ ነው
ፍቅሩም ለልጅ ልጅ ነው።(4)