Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 288 ተመስገን እግዚአብሔር ሆይ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 288 ተመስገን እግዚአብሔር ሆይ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ተመስገን እግዚአብሔር ሆይ
ስለ ውለታህ ሁሉ፥
የሱስ ከኔ ጋር ሆኖልኝ፥
በቸርነት አደለኝ።
በደስታ በኀዘን ጊዜ፥
ሳይለይ ከቶ ከኔ።
ተመስገን በልቅሶ ፈንታ፥
ሰላሙን ስለ ተካ።
፪፡ ተመስገን ለጸሎት መልሶች
ስለ – ምሕረትህ ሁሉ።
ማእበሉን ስላሻገርኸኝ፥
በጸጋህ ስላቆምኸኝ።
በደስታ በኀዘን ጊዜ፥
በአንተ ተደግፌ።
ተመስገን ለጸጋህ ሙላት፥
ተመስገን ስለ ፍቅርህ።
፫፡ ተመስገን ስለ ሞገስህ
በምቾት በችግርም።
ስለ ሰጠኸኝ በረከት፥
ተስፋህ ስለሚፈጸም።
ዘወትር የማትለየኝ፥
ሁል ጊዜ የምትመራኝ።
ተመስገን እግዚአብሔር ሆይ፥
ተመስገን ለዘላለም።

Exit mobile version