Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 286 ዓላማ ይዞ የተሰለፈ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 286 ዓላማ ይዞ የተሰለፈ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ዓላማ ይዞ የተሰለፈ
የሚያስፈራ ያንተ ሠራዊት፥
ጠላቱን ሁሉ እያሸነፈ፥
ባንተ መሪነት ቀንና ሌሊት።
ባሕር ተሸግሮ በምድረ በዳ፥
ጊንጡን ረጋግጦ፥
ጥቂቱ ሕዝብህ ካንተ ጋር ወጥቶ፥
ርስቱን ጨበጠ ከብዙ በልጦ።
ሕዝብን አበዛህ ሕዝብን አበዛህ፥
ያገሪቱንም ወሰን አሰፋህ፥
የማዳን እጅህን ለኛ ዘረጋህ።
ሕዝብን አበዛህ ሕዝብን አበዛህ፥
ያገሪቱንም ወሰን አሰፋህ፥
የማዳን እጅህን ለኛ ዘረጋህ።
፪፡ የሰናፍጭዋን ቅንጣት ቢዘራ
ጌታ በምድር እንድትበዛ፥
ያ ጉልበተኛ መጥቶ ረገጣት፥
የማትበቅል መስላው ፈዛዛ፥
ግን አልተሳካም አምልጣ ወጣች
ሄደች አደገች፥
ጌታ ይመስገን ድንበርዋ ሰፋ፥
ለደካከሙት መጠለያ ሆነች።
ሕዝብን አበዛህ . . .።
፫፡ ኦ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ
እያሸነፈ ዘላለም ነዋሪ፥
እንደ አምላካችን ያለ ታዳጊ፥
ከቶ የታለ ተወዳዳሪ።
ጩኸትን ሰምቶ ምስኪን ድሆችን፥
ዘይት የሚቀባ፥
ባደባባዩ በቤቱ ተክሎ
የሚያለመልም እንደዘንባባ።
ሕዝብን አበዛህ . . .።

Exit mobile version