መዝሙር 281 ነፍሴ ሆይ፥ ጌታን ባረኪ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ነፍሴ ሆይ፥ ጌታን ባረኪ
ድንቅ ሥራውን አትርሺ፥
በፈሰሰው ቅዱስ ደሙ፥
ከኃጢአት አነጻሽ።
ነጽቻለሁ ነጽቻለሁ፥
በፈሰሰልኝ ክቡር ደሙ ነጽቻለሁ።
፪፡ እምነታችንን አበርታ
የመንፈስን ኃይል ስጠን፥
ደስ ይበለን እንወድስህ፥
ስለ ታላቅ ምሕረትህ።
እንወድሰው እንወድሰው፥
እንወድሰው ስለ ታላ – ቁ ምሕረቱ።
፫፡ ሕይወታችንን አድሰህ
ዕለት ዕለት ባርከን፥
በማይለወጠው ፍቅርህ፥
አፍስስልን ጸጋህን።
ሰላምህን ስጠን ሰላምህን ስጠን፥
እውነተኛው ሰላም ይሚገኝ ከአንተ ነው።
