መዝሙር 280 ሁሉን የፈጠረ አምላክ ይመስገን የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ሁሉን የፈጠረ አምላክ ይመስገን
ዓለምን ለማዳን ልጁን ለሰጠን።
እኛን ሊዋጀን ሕይወቱን ሠዋልን
የደኅንነት መንገድ ከፈተልን።
ተመስገን ተመስገን ምድር ቃሉን ስሚ
ተመስገን ተመስገን ሰው ሁሉ ይደሰት
ወደ አብ ቀርበናል በኢየሱስ ክርስቶስ
ሁሉን ለፈጸመው ምስጋና ይድረስ።
፪፡ ለፍጹም ደኅንነት በደሙ ገዛን
በስሙ ለምናምን ተስፋ ተሰጠን።
በደለኛ በንስሐ ሲቀርበው
በቅጽበት ከኢየሱስ ያገኛል ምሕረት።
ተመስገን ተመስገን . . .።
፫፡ ታላቅ ሥራ ሠርቶ አስተምሮናል
ደስታችን ታላቅ ነው በርሱ ድነናል።
በድንቅ ሥራው ነጽተን ከፍ ከፍ ብለናል
በሰላም ከኢየሱስ ጋር እንኖራለን።
ተመስገን ተመስገን . . .።
