Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 276 ነፍሴ ሆይ አምላክን ባርኪ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 276 ነፍሴ ሆይ አምላክን ባርኪ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ነፍሴ ሆይ አምላክን ባርኪ
ኃጢአትሽን ሁሉ ተወልሽ፥
ምስጋናውንም አትርሺ፥
ሕይወትሽንም ተቤዥሽ።
፪፡ ደዌሽን ሀሉ ፈወሰሽ
በጸጋውና በምሕረቱ፤
ከዘላለም ሞት ከለለሽ፥
እንድትኖሪ ለክብሩ።
፫፡ ያንቺ ሕይወት እንዲታደስ
በጎ ነገር አጠገበሽ፤
ቀድሶ በመንፈስ ቅዱስ፥
ወደ ሰማይ ክብሩ አስገባሽ።
፬፡ በምሕረቱ ደስ ይበልሽ
በጽድቅ በምሕረት ጠርቶሻል፤
በታላቅ ደስታ ሊያኖርሽ፥
አንድ ልጁን ቤዛ ሰጥቶሻል።
፭፡ ኃዘንና ጭንቀትሽን
በሥቃይ አጥፍቶልሻል፤
ሕይወቱን ሠውቶልሻል፥
ቅዱስ ደሙ ፈውሶሻል።
፮፡ እንግዲህ አትጨነቂ
አምላክሽ ከአንቺ ጋር ነው፥
መከራ አይድረስብሽ፥
የሱስ በጸጋው አዳነሽ።

Exit mobile version