Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 272 የአምላኬን ውለታ ሁሉ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 272 የአምላኬን ውለታ ሁሉ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ የአምላኬን ውለታ ሁሉ
ልቆጥረው ያቅተኛል፥
ከላይ እንደወረደው ጠሉ፥
በሁሉ ተትረፍርፎአል።
የአምላኬን ውለታ ሁሉ፥
ልቆጥረው ያቅተኛል።
፪፡ ሳይታሰብ ሳይመዘን ይቀራል
የፍቅሩ የጸጋውም ብዛት፥
በጨለማ ውስጥ ግን ያበራል፥
በሌትም ይሰጣል ንጋት።
ሳይታሰብ ሳይመዘን ይቀራል፥
የፍቅሩ የጸጋውም ብዛት።
፫፡ ልመዝነው ከቶ ባይቻለኝ
ይልቅ ላመሰግነው ነኝ፥
የውለታው ትሩፋት ካለኝ፥
የፍቅሩ ብርታት ታወቀኝ።
ልመዝነው ከቶ ባይቻለኝ፥
ይልቅ ላመሰግነው ነኝ።

Exit mobile version