መዝሙር 27 ምእመናን ሁሉ ኑ ወደ ቤተልሔም የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ምእመናን ሁሉ ኑ ወደ ቤተልሔም፤
በግርግም ለተኛው ስገዱለት፤
ኑ አክብሩት ምስጋናም አቅርቡለት።
በደስታ እናክብረው፤
በደስታ እናክብረው፤
በደስታ እናክብረው፤
ክርስቶስ ጌታን።
፪፡ የሰማይ ሠራዊት በደስታ ዘመሩ፤
በአርያም ዘመሩ ለየሱስ ክብር፤
ለአምላክ በሰማይ ምስጋና ይሁን።
በደስታ . . .።
፫፡ ሥጋ ለብሶ ስለ እኛ ተወለደ፤
ያብም ክምር በርሱ ተገለጠ፤
እንስገድለት በበረት ለተኛው።
በደስታ . . .።
፬፡ ወደኛ የመጣው ያምላክ ልጅ ይመስገን፤
በውርደት ስለኛ ተወልዶአል፤
ምስጋና ክብር ስግደት ይገባዋል።
በደስታ . . .።