Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 268 ኑ እናንት ሰዎች የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 268 ኑ እናንት ሰዎች የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ኑ እናንት ሰዎች
ጌታን አመስግኑ።
አብራችሁም ልጆች
ጸጋውን ተቀበሉ
ፍቅሩን ተናገሩ።
፪፡ ሰማይና ምድር
በግርማው ሲሞላ
ራሱን አዋርዶ
በትሕትና መጣ
ስለኛም ተወጋ።
፫፡ ሕማማችንን
እርሱ ተሸከመ።
ኃጢአታችንን
ሞቶ አስወገደ
ለኛም ሰላም ሰጠን።
፬፡ እኛን ሊያድን
ቅዱሱ ቆሰለ
ለርሱ ሊዋጀን
እጅግ ተሠቃየ
በመስቀል ላይ ሞተ።
፭፡ በቃል በሥራ
የሱስን እናክብር።
በሞቀ ደስታ
ስለ አምላክ ፍቅር
መዝሙር እንዘምር።

Exit mobile version