መዝሙር 266 ደስ እንዲለን ይገባናል የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ደስ እንዲለን ይገባናል
ባገኘነው ድንቅ ነገር
አምላክ አሁን ይምረናል
ፍርዳችን ሞት የነበር።
ሊምረን ስለ ወደደ
አንድያ ልጁን ሰደደ
ይህም ደስታችን ሆነ።
፪፡ ተስፋ ስቆርጥም ከጥፋት
መዳኔ ስላልታየኝ።
አምላክ በምሕረቱ ብዛት
በአባት ፍቅር አየኝ።
በኃጢአቴም ታስሬ
ሳለሁ ተሰማኝ ያባቴ
ዘላለማዊ ምሕረት።
፫፡ እንዲህ ብሎ ተናገረ
እራራላቸዋለሁ።
በኃጢአት የጠፉትን
ለልጄ እሰጣለሁ።
በደሙ ከዘላለም ሞት
ሊያድናቸው ሰደድኩት
ሊሆንላቸውም ሕይወት።
፬፡ አባቱ እንደ ፈቀደ
ወልድ ታዘዘ በፍቅሩ።
ከሰውም ሥጋ ተዋሐደ
የሰማይ ክብሩን ትቶ።
ሕግ በኔ እንደ ፈረደ
የኔን ቅጣት ተቀበለ።
እኔን ነጻ አወጣኝ።
