Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 264 ወዳጄ ነው የሱስ ክርስቶስ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 264 ወዳጄ ነው የሱስ ክርስቶስ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ወዳጄ ነው የሱስ ክርስቶስ
የሁሉ ጌታና ንጉሥ፥
እርሱም ለኔ ሲል ሞተልኝ፥
ከኃጢአት ሊያድነኝ።
ሃሌ ሉያ ደስ ይበለኝ፤
ለዘለዓለም የየሱስ ነኝ፤
እጄን ይዞ ይመራኛል፤
ወደ ሰማይ ያደርሰኛል።
፪፡ በሥልጣኑ ለዘለዓለም
ይነግሣል በሁሉ ዓለም፤
በኃይሉ እታመናለሁ፥
ከእንግዲህ ምን እፈራለሁ?
ሃሌ ሉያ . . .።
፫፡ የርሱም ፍቅር ያድነኛል፤
ዕረፍትንም ይሰጠኛል።
ልቤን በደስታ ይሞላል፤
መንገዴን ያቀናልኛል።
ሃሌ ሉያ . . .።
፬፡ ይህ ወዳጄ፥ ወንድሜ ሆይ፥
ይጠራሃል አትሰማም ወይ?
አሁን ቅረብ፥ አትፍራ ና፤
ጸጋን ይሰጥሃልና።
ሃሌ ሉያ . . .።

Exit mobile version