Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 259 ክብር ይገባሃል የኛ አምላክ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 259 ክብር ይገባሃል የኛ አምላክ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

ክብር ይገባሃል የኛ አምላክ
ክብር ይገባሃል የኛ አምላክ
ዙፋንም ምስጋናም ላንተ ነው
ዙፋንም ምስጋናም ላንተ ነው
ክብር ሃሌ ሉያ፥ ክብር ሃሌ ሉያ፥
ክብር ሃሌ ሉያ፥ ክብር ሃሌ ሉያ።
፩፡ እግዚአብሔር ነገሠ ክብር ለበሰ
ታጠቀ ኃይልንም ለበሰ።
ዓለምን አጸናት አቆማት፥
ምሕረትህ ጽድቅ ዘላለማዊት።
ክብር ይገባሃል . . .።
፪፡ ዘላለማዊ አምላክ አንተ ነህ
ዝግጁ ነው ከጥንት ዙፋንህ።
ወንዞች ከፍ አረጉ ድምጻቸውን፥
ተራሮችም ጤሱ ሰጡ ክብርን።
ክብር ይገባሃል . . .።
፫፡ ከብዙ ውሆችም ድምፅ ይልቅ
ከታላቅ ሞገድም ድምፅ ይልቅ፥
ጌታችን አንተ ነህ ኃያል ድንቅ፥
ምስክርህ ታማኝ አንተ ታላቅ።
ክብር ይገባሃል . . .።

Exit mobile version