መዝሙር 257 ክብር ይሁን ለአምላካችን የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ክብር ይሁን ለአምላካችን
ስለማይናወጥ ተስፋው።
በእምነት በርሱ ከጸናን፥
ይመግበናል መናውን።
፪፡ ጊዜው ሲደርስ እወርሳለሁ
ያንን ብፁዕ ከነዓኔን።
ሰንደቅ አላማዬን ይዤ፥
ድሉን ተጐናጽፌ።
፫፡ ሃሌ ሉያ ልዑል አምላክ
ሕዝብህን ጠብቀሃል።
በምትጠራኝም ጊዜ፥
በመቅደስህ እሰግዳለሁ።
