መዝሙር 256 ደስተኞች ሁኑ በዓለም ሙሉ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ደስተኞች ሁኑ በዓለም ሙሉ
ተደሰቱ ወጣት ሴት ወንዶች ሁሉ።
ተቀኙለት በእምቢልታ በበገና
ጌታን አገልግሉ በዕልልታ።
ተቀኙለት በእምቢልታ በበገና።
ጌታን አገልግሉ በእልልታ።
፪፡ በቆየው የአምልኮ ሥርዓት
አክብሩ በደስታ የምስጋናን በዓል።
በግርማው በወጣው በሠራዊት ጌታ
አዜመ ዳዊት በታቦቱ ፊት።
በግርማው በወጣው በሠራዊት ጌታ
አዜመ ዳዊት በታቦቱ ፊት።
፫፡ በሲኦል ሸለቆ ይበዛዋል ልቅሶ
ደስታ ግን ይንሰራፋል በሰማይ።
ያለቅሳሉ የሚሠሩ ክፋት
ይደሰታሉ የሠሩ ሠናይ።
ያለቅሳሉ የሚሠሩ ክፋት
ይደሰታሉ የሠሩ ሠናይ።
