Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 255 የሱስ አዳኜ ወደ ቤት ልሔም የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 255 የሱስ አዳኜ ወደ ቤት ልሔም የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ የሱስ አዳኜ ወደ ቤት ልሔም
መጥቶ በበረት ውስጥ ተወለደ፥
እኔን ሊፈልግ ከላይ ወረደ።
ስሙ ይክበር ይክበር፥
ስሙ ይክበር ይክ – በር፥(2)
እኔን ሊፈልግ ከላይ ወረደ፥
ስሙ ይክበር ይክበር።
፪፡ የሱስ በቀራንዮ መስቀል ላይ
ዕዳዬን ከፍሎ ነፍሴን አዳነ፥
አስደናቂ ነው እንዴት ፈቀደ።
ለኔ ሊሞት ሊሞት፥
ለኔ ሊሞት ሊ – ሞት፥(2)
አስደናቂ ነው እንዴት ፈቀደ፥
ለኔ ሊሞት ሊሞት።
፫፡ የሱስ አዳኜ አለው ቸርነት
ከመንጋው ጠፍቼ ስንከራተት፥
ነፍሴን ለማዳን ሆኖ መሥዋዕት።
አውጥቶኛል ከሞት፥
አውጥቶኛል ከሞ – ት፥(2)
ነፍሴን ለማዳን ሆኖ መሥዋዕት፥
አውጥቶኛል ከሞት።
፬፡ የሱስ አዳኜ አዎን ይመለሳል
ተስፋው ለኔ ጽኑ አለኝታ ነው።
እንዳረገ ሲመለስ ከሰማይ
አየዋለሁ በክብር
አየዋለሁ በክ – ብር፥(2)
እንዳረገ ሲመለስ ከሰማይ
አየዋለሁ በክብር።

Exit mobile version