Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 246 ነፍሴ አምላክሽን አክብሪ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 246 ነፍሴ አምላክሽን አክብሪ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ነፍሴ አምላክሽን አክብሪ
በጎ ሥራውን አታቃልዪ።
በደልሽን ይቅር ይላል
ጉድለትሽን ያሟላል።
ነፍሴ ነፍሴ ለጌታ ስገጂ
ዘምሪ ዘምሪ ለአምላክሽ ተቀኝ።
፪፡ በጸጋው ተከልለሽ
ከጥፋትሽ ትድኛለሽ
ሁሉን ቻይ ነውና ጌታ
ለተገፉት ይፈርዳል።
ነፍሴ . . .።
፫፡ እንደ ሰማይ ከዋክብት
ምሕረቱ እጅግ የበዛ ነው።
ስሙን ለሚያከብሩ ሁሉ
ጸጋውን ይሰጣቸዋል።
ነፍሴ . . .።
፬፡ አባት ለልጆቹ እንደሚራራ
ሰማያዊ አባታችን።
በርሱ ለሚያምኑት ሁሉ
እርሱ ያድናቸዋል።
ነፍሴ . . .።
፭፡ እናንት ታዛዥ መላእክት
ለአምላክ አቅርቡ ስብሐት።
ኑ አክብሩት ፍጥረታት ሁሉ፥
ለታላቅ ክብሩ ዘምሩ።
ነፍሴ . . .።

Exit mobile version