መዝሙር 244 ጌታ አምላኬ እንዴት እገረማለሁ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ጌታ አምላኬ እንዴት እገረማለሁ
የጆችህን ፍጥረት ሳስብ ሳለሁ
ነጎድጓድን ስሰማ ሳይ ከዋክብትን
በሕዋህ ውስጥ ታየኝ ያንተ ስልጣን።
ነፍሴ ላንተ መዝሙር ታዜማለች
ኃያል ግሩም ታላቅ አምላክ።
ነፍሴ ላንተ መዝሙር ታዜማለች
ኃያል ግሩም ታላቅ አምላክ።
፪፡ ጥቅጥቅ ባለው በደን ውስጥ ስመላለስ
የወፎችን ዝማሬ ስሰማ፥
ሳይ ወደ ታች ከፍ ካለው ተራራ ላይ
ምንጩ ሲፈልቅ ነፋሱም ሽው ሲል።
ነፈሴ ላንተ . . .።
፫፡ ሳስብ ሳለሁ አብ ለልጁ ሳይሳሳ
እንደላከው ሊሞት በኔ ፈንታ።
በመስቀል ላይ በደሌን ተሸክሞ፥
ተሰቃየ ስለኔ ኃጢአት።
ነፍሴ ላንተ . . .።
፬፡ ክርስቶስ የሱስ በታላቅ ክብር መጥቶ
ይዞኝ ሲሄድ ደስታዬ እንዴት ይሆን?
እዚያም ለርሱ በምሰጋና እሰግዳለሁ፥
ለታላቁ ግሩም ኃያል አምላክ።
ነፍሴ ላንተ . . .።
