Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 241 ለአምላክ ዘምሩ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 241 ለአምላክ ዘምሩ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ለአምላክ ዘምሩ
በእርሱ ደስ ይበለን።
በማይነገር ፍቅሩ
ግሩም ውለታን ዋለልን።
ከእናት ማኅፀን
በምሕረት እስካሁን
ዘወትር ሲጠብቀን
ሠራልን መልካሙን።
፪፡ የጸጋ አምላክን
ዞትር እንድንፈራ
የርሱን መንፈስ ይስጠን
በርሱ እንድንመራ።
የምሕረት አምላክም
ይስጠነ ምሕረቱን።
እስከ ዘላለምም።
ከእኛ ጋር ይሁን።
፫፡ ሰርክ እናመስግንህ
ኦ አብ፥ ኦ ወልድ፥ ኦ መንፈስ፤
ዘላለም አምላክ ነህ
ኦ አንተ ሥሉስ ቅዱስ።
ለቅድስት ሥላሤ
ለሦስቱ አካላት።
እናቅርብ ውዳሴ
እናቅርብም ስብሐት።

Exit mobile version