Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 240 ያን ክቡር ዕንቁ አገኘሁ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 240 ያን ክቡር ዕንቁ አገኘሁ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ያን ክቡር ዕንቁ አገኘሁ፤
እርሱም ጌታ የሱስ።
አገኘው ዘንድ ተመኘሁ፥
በልቤ እንዲነግሥ።
፪፡ ከአምላክ ጋር አስታረቀኝ።
የሕይወትንም ቃል
በመንፈሱ ገለጠልኝ፤
በልቤም ነግሦአል።
፫፡ የጌቶች ሁሉ ጌታ ነው፤
የነገሥታት ንጉሥ።
ቀንበሩንም ብሸከመው፥
በእውነትም መልካም ነው።
፬፡ ድኃ ብሆን ችግረኛም
ተስፋ ይሆነኛል።
በኃጢአት ስጨነቅም
ስርየት ይሰጠኛል።
፭፡ እርሱ ነው ጽድቄ ሕይወቴም
ሰላሜ ጤናዬም።
እርሱ ነው ደኅንነቴም
ደስታዬ ብርታቴ።
፮፡ የሱስ ሆይ የልቤ ዕረፍት
የነፍሴም መድኃኒት፥
አልፋ ኦሜጋ ለኔ ሁን
ሁሉ በሁሉ ሁን።

Exit mobile version