Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 24 እረኞች መንጋቸውን የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 24 እረኞች መንጋቸውን የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ እረኞች መንጋቸውን
ሌሊት ነቅተው ሲጠባበቁ፥
የጌታን መልአክ ክብር አዩ
በዙሪያቸው ደምቆ በዙሪያቸው ደምቆ።(2)
፪፡ እርሱም አላቸው አትፍሩ
አትደናገጡ፥
አለኝ መልካም የምሥራች
ለሰው ልጆች ሁሉ ለሰው ልጆች ሁሉ።(2)
፫፡ ዛሬ በዳዊት ቤት ለላንት
ከዘሩም ተወልዶአል፥
እርሱም ክርስቶስ ጌታችን ነው
ምልክቱም ይህ ነው ምልክቱም ይህ ነው።(2)
፬፡ ክብር ይሁን ላምላክ በላይ
ሰላምም በምድር
መልካም ፈቃዱ ከሰማያት
በዓለም ላይ ይስፈር በዓለም ላይ ይስፈር።(2)

Exit mobile version