Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 239 ቅዱስ ቅዱስ ቀዱስ እግዚአብሔር የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 239 ቅዱስ ቅዱስ ቀዱስ እግዚአብሔር የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
ስብሐት ላንተ በሰማይ ለምትኖር።
ይገባናል ምስጋናህን ልንዘምር፥
በልባችን ቅዱስ ቃልህ ይደር።
፪፡ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
ነዋሪ አምላክ በሰማይ በምድር።
የምታቀል የኃጢአትን ቀንበር፥
በምሕረትህ ስጠን ሰላም ፍቅር።
፫፡ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
ርኅሩኅ አምላክ በደልን የሚምር።
ስንለምንህ በኤድን ገነት ልንኖር፥
አካፍለነ ከብፁዓን ማኅበር።

Exit mobile version