መዝሙር 236 ሕዝቦች ሆይ ደስ ይበላችሁ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ሕዝቦች ሆይ፥ ደስ ይበላችሁ
አምላክን አመስግኑ።
በኪዳኑ የቆማችሁ፥
በአንድነት ቅረቡ።
ቅረቡ በእልልታ፥
ዘምሩ ለቸር ጌታ።
ቅረቡ በእልልታ፥
ዘምሩ ለቸር ጌታ።
፪፡ ዘምሩለት በደጆቹ
አምልኩት በመቅደሱ።
ካገር ሁሉ ተከማቹ፥
ቸሩን ጌታ ወድሱ።
ርኅሩኅ ሆኖ ይጸናል፥
ሁልጊዜም ይመራናል።
ርኅሩኅ ሆኖ ይጸናል፥
ሁልጊዜም ይመራናል።
፫፡ እርሱ ነው የፈጠረነ
መድኅን የላከልነ።
ከዘላለም ፍርድ ያዳነን፥
ጽድቅን ያጎናጸፈን።
ለሰማያዊው ደስታ፥
ሆኖልናል አለኝታ።
ለሰማያዊው ደስታ፥
ሆኖልናል አለኝታ።
