መዝሙር 23 የጌታ ኢየሱስ መንግሥት ሲመሰረት የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የጌታ ኢየሱስ መንግሥት ሲመሰረት
የሰናፍጭ ፍሬን ይመስላል
የዓለም ሙሉ መድኃኒት ሆኖ
በበረት ውስጥ ተወለደ።
፪፡ መላእክቱም በላይ በጣም ደስ አላቸው
አምላክን እያወደሱ
የመድኅን ልደት የደስታ መልእክት
ለኃጢአተኞች ነገሩ።
፫፡ ደማቁ ኮከብ ከላይ እያበራ
ወደ ቤተልሔም መራቸው
የታደሉትን አደረሳቸው
ወደ ደማቅ ብርሃን ተስፋ።
፬፡ እየናፈቁ የምሥራቅ ነገሥታት
ደርሰው ሰገዱ ለሕፃኑ፥
ከርቤና ዕጣን ወርቅን አመጡ፥
አምላክን እያወደሱ።
፭፡ የምድር ሕዝቦች ወንጌልን ስሙ
የሰላም ንጉሥ አማኑኤል
ክብር ምሥጋና ስግደትም ሁሉ
ይሁንለት ለዘለዓለም።