Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 228 እውነት ካንተ ጋር ትሁን የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 228 እውነት ካንተ ጋር ትሁን የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ እውነት ካንተ ጋር ትሁን እውነት ተናገር
ከእውነት አትለያይ እውነት ተናገር።
ከልጅነት ጀምረህ ብቻ እውነት ተናገር
እውነት ይዘህ እደግ እውነት ተናገር።
፪፡ ዓላማህ አውነት ይሁን እውነት ተናገር
ውሸትን ካንተ አርቅ እውነት ተናገር።
በውሸት ብታመልጥም ውርደት
ይከተልሃል
በእውነት ጽና በርታ እውነት ተናገር።
፫፡ ተጸጸት በጥፋትህ እውነት ተናገር
አትሸነፍ ለውሸት እውነት ተናገር።
እውነትን ጓድህ አርጋት ሁሌም
እውነት ተናገር
ክብር ትሆንሃለች እውነት ተናገር።

Exit mobile version