መዝሙር 226 የኢየሩሳሌም ልጆች የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የኢየሩሳሌም ልጆች
ለየሱስ ዘመሩለት።
እኛም በያለንበት፥
እንደነርሱ እንዘምር።
ዘምሩ ስሙን አመስግኑ፥(2)
ሆሣዕና ሆሣዕና ሆሣዕና፥
የዳዊት ልጅ።
፪፡ ንጉሥ ዳዊትም ያለው
ትንቢት ተፈጸመ።
ከሕፃናት አፍ ደግሞ
ምስጋናን አዘጋጀህ።
ዘምሩ ስሙን . . .።
፫፡ ፍጥረት ሁሉ ተነሡ
ባንድነት ዘምሩለት።
እስከ ሰማይ እስኪደርስ፥
ድምፃችሁን ከፍ አድርጉ።
ዘምሩ ስሙን . . .።
