መዝሙር 224 ደስ ብሎኛል የሱስ ይወደኛል የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ደስ ብሎኛል የሱስ ይወደኛል
በቅዱስ መጽሐፍ ገልጦ ነግሮኛል።
የርሱን ፍቅር ተረድቼዋለሁ
ከሁሉ የሚልጥ ተቀብያለሁ።
ፍቅሩ ከባሕር የጠለቀ ነው
ደስ ብሎኛል ደስ ብሉኛል።
የሱስ በፍቅሩ ዋጅቶኛል
በፍቅሩም ገዝቶኛል።
፪፡ ስለ ወደደኝ ወድጄዋለሁ
በርሱ ክብር እኔ ከብሬአለሁ።
በመስቀል ሞት ፍቅሩን የገለጠው
እኔን ጥፉ ልጁን ለማዳን ነው።
ፍቅሩ ከባሕር . . .።
፫፡ በርሱ አለኝታ ተባርኬአለሁ
በፍቅሩ ሕይወት አግኝቻለሁ።
ጠላት ካጠገቤ ርቆልኛል
ጌታ አሸንፎት ደስ ብሎኛል።
ፍቅሩ ከባሕር . . .።
፬፡ በደስታ መንፈስ የምዘምረው
ንጉሤን በክብር በማየቴ ነው።
እስከ ፍጻሜ ይህ ነው መዝሙሬ
እየተመገብሁ የወንጌልን ፍሬ።
