መዝሙር 221 የሱስ እንደ ወደደኝ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የሱስ እንደ ወደደኝ
ቅዱስ ወንጌል ነገረኝ
የርሱ ናቸው ታናሾች
ኃይልም ነው ለደካሞች።
እኔን ይወዳል
እኔን ይወዳል
እንደሚወደኝ
ወንጌሉ ነገረኝ።
፪፡ የሱስ ስለወደደኝ
በሰማይ ልገባ ነኝ።
በደሌን ይቅር ይላል
ትንሽ ልጁን ያቅፋል።
እኔን ይወዳል . . .።
፫፡ ኢየሱስ አይተወኝም
ቤቱን አይዘጋብኝም።
ሁልጊዜ ይረዳኛል።
በእጁም ይመራኛል
እኔን ይወዳል . . .።
