መዝሙር 22 የተባረከች ናት የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የተባረከች ናት
የተቀደሰች ናት፥
ታላቅ ደስታ የልደት ቀን
አቅርቡ ክብር በሁሉ ምድር
ያምላክን ፍቅር እናመሰግን።
፪፡ መሢሕ መጣልን
ሕዝቡን ሊያድን
ክርስቶስ ጌታ ከእሴይ ሥር
ዕርቅን አመጣ ተገኘ ነፃ
ሐሴትን አድርጊ ነፍሴ ሆይ።
፫፡ አምላክ ይመስገን
ስለሚሰጠን፥
ታላቅ ጸጋ በቸር ልጁ።
ወንድም ሆነልን ደጅ ከፈተልን።
አደረገንም ወገኖቹ።
