መዝሙር 217 የሱስ ሆይ ወዳንተ ዓይኔን አነሣለሁ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ የሱስ ሆይ ወዳንተ ዓይኔን አነሣለሁ
የአምላክ በግ ሁነህ ኃጢአቴን አጠብከው።
፪፡ ተሠቃየህ ለኔ ሕይወትን ለመስጠት
ሸክሜን ተሸክመህ አዳንኸኝ ከጥፋት።
፫፡ በኔ የጀመርኸውን ስለምትፈጽመው
እንደ ቃልህ ተስፋ ተመስገን ጌታዬ።
፬፡ እጅግ የከበረ ዓይን ፍጹም ያላየው
ቦታ አዘጋጀህ በሰማያዊ ቤት።
፭፡ የአባታችን ሥራ ጸጋና ፍቅር ነው
የኢየሱስም ፍቅር ዘላለማዊ ነው።
፮፡ ስሰናበት ሳለሁ ከዚህ ከንግድነት
ኢየሱስ አንተ ምራኝ ወደ ሰማዩ ቤት።