መዝሙር 215 ከኔ ጋር ሁን ዘመኔ ገሥግሦአል የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ከኔ ጋር ሁን ዘመኔ ገሥግሦአል
ከኔ ጋር ሁን ጨለማውም ከብዶአል።
ረጅዎቼ ሁሉ ከኔ ሲርቁ
ቸል የማትል ጌታ ከኔ ጋር ሁን።
፪፡ አለኝታህን እማጠናለሁ
በጸጋህ ሸፍነኝ ከመዓቱ።
እንደ አንተ ማን ይሆንልኛል
የሕይወቴ ብርሃን ከኔ ጋር ሁን።
፫፡ አንተ ካለህ ክፉውን አልፈራም
ስሠቃይ ሳለቅስም አይመረኝም።
የሞት ሾህ የሲኦል ድል ተሻረ
አሸናፊው ጌታ ከኔ ጋር ሁን።
፬፡ መስቀልህን ልይ ዓይኔ ሳይዘጋ
ብርሃን ሆነህ መንገዴንም አብራ።
ምድር ሲጨልም ሰማይ ሲበራ
በሞት በሕይወት ሁን ከኔ ጋራ።
