መዝሙር 214 አንድ ቀን ይመጣል ልብ የማይዝልበት የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ አንድ ቀን ይመጣል ልብ የማይዝልበት
ደመናና ጭጋግ ልቅሶም የሌለበት።
በወርቃማው ምድር ሁሉ ሰላም ሆኖ
ምን ዓይነት ክቡር ቀን ይሆናል።
ምን ዓይነት የከበረ ቀን ይሆን ጌታን ሳይ
ፊቱን ስመለከት በጸጋው ያዳነኝን
በእጁ ይዞኝ ስሄድ ወደ ተስፋው አገር
ምን ዓይነት ክቡር ቀን ይሆናል።
፪፡ ኀዘን የለም ጭንቀት ልቅሶ የለም ጩኸት
ሕመም የለም ስሜት ንዴት አይኖር መጥላት
ከሞተለኝ ጋራ ለዘላለም መኖር
ምን ዓይነት ክቡር ቀን ይሆናል።
ምን ዓይነት . . .።
፫፡ ሞት የለም በዚያ ድካም መንገላታት
ረሀብና ጥማት የለም የራስ ምታት።
ፈዋሹ መድኅኔ ይኖራል ከእኔ ጋር
ምን ዓይነት ክቡር ቀን ይሆናል።
ምን ዓይነት . . .።
