መዝሙር 211 ሰባኪው አለ፥ ከንቱ ነው የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ሰባኪው አለ፥ ከንቱ ነው
ከሰማይ በታች የሚሠራው፤
ደስ የሚለውና የሚያዝነው
ሁሉም በቶሎ ሊያልፍ ነው።
ከንቱ ነው፥ ከንቱ ነው
ሰባኪው አለ ከንቱ ነው።
ከንቱ ነው፥ ከንቱ ነው
የዚህ ዓለም ሀብት
ከንቱ ነው።
፪፡ እንደ ኗሪ ሰው ብዙ ዓመት
ስደክም በዚህ ዓለም ንብረት፥
ና ብለህ ብትጠራኝ በቅፅበት፥
ምን ልመልስ ነኝ በአንተ ፊት።
ከንቱ ነው . . .።
፫፡ ባለ ጸጋ ሆይ ለምንህ
መዝገብን ትሰበስባለህ?
ዛሬ ማታ ትፈለጋለህ፥
ልትሄድ በሞት ኃይል ተይዘህ።
ከንቱ ነው . . .።
፬፡ ሰው ሁሉ ከንቱን ይመስላል፤
ዘመኑም እንደ ጥላ ያልፋል፤
በቅፅበት አበባው ይረግፋል፤
መታሰብያውም ይጠፋል።
ከንቱ ነው . . .።