መዝሙር 210 ቢኖር አምላክ በቤታችን የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ቢኖር አምላክ በቤታችን
ፍቅሩን ይሰጠናል።
የኛን ምኞትና ጸሎት
በደስታ ያደምጣል።
፪፡ ጌታ የሱስ ያለበት ቤት
ሰላም ነው ለሁሉ።
ሕጉ ሆኖ ብርሃናቸው
ኃይሉ ብርታታቸው።
፫፡ ጸሎት የሚሰማበት ቤት
ደስታ ሰላም አለው።
ልዑል አምላክ ለማደሪው
ባርኮ ያደረገው።
፬፡ አምላክ ሆይ አስማማን አሁን
ሰላምን ለማፍራት
ባንተ ይማረክ ልባችን
ስምህም ይክበር አሜን።