Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 209 ደስ ይበላችሁ ሙሽሮች የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 209 ደስ ይበላችሁ ሙሽሮች የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ደስ ይበላችሁ ሙሽሮች አምላክን አመስግኑ
በመንገዱ እንዲመራችሁ በተስፋው ተማመኑ።
ደስ ይበላችሁ በጌታ ቤታችሁን ይሙላ ደስታ
በፍቅሩ ያሞቃችኋል ከእናንተ ጋር ይኖራል።
፪፡ ደስ ይበላችሁ ሙሽሮች በጸሎት ጽኑ በርቱ
ፈተና ቢመጣባችሁ በርሱ ኃይል አሸንፉ።
ይቅር ለመባባል ትጉ በፈቃዱ ተመሩ
በቃል ኪዳናችሁ ጽኑ የጌታን ቃል ጠብቁ።
፫፡ ደስ ይበላችሁ ሙሽሮች በኢየሱስ ተመሥረቱ
ምሣሌውን ተከተሉ ትሕትናውን ልበሱ።
በምሕረቱ ይጐብኛችሁ ጸጋውንም ይስጣችሁ
ከክፉ ይጠብቃችሁ ሰላሙንም ይስጣችሁ።
፬፡ ይባርካችሁ ይጠብቃችሁ ፊቱንም ያብራላችሁ
ሞገሱን ያጐናጽፋችሁ በመንፈሱ ይምራችሁ።
በክንፉ ይጋርዳችሁ ብርሃን ይሁንላችሁ
እስከ ፍጻሜ ይርዳችሁ ፈቃዱ ይሁን አሜን።

Exit mobile version