መዝሙር 208 መልካም ጋብቻ ይሁንላችሁ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ መልካም ጋብቻ ይሁንላችሁ
ጌታ ይባርካችሁ።
ባላችሁ ነገር ደስ ይበላችሁ
ሰላሙን ይስጣችሁ።
ጌታ የሱስን መሪ አድርጉ
በማይለወጥ መዋደድ ጸኑ።
የሰማይ አፍቃሪ አባታችሁ
ፍቅሩን ያብዛላችሁ አሜን።
የሰማይ አፍቃሪ አባታችሁ
ፍቅሩን ያብዛላችሁ አሜን።
፪፡ እረኛችሁን መምሰል አትርሱ
ትሕትናን ልበሱ
እርሱ እራሱን ዝቅ ዝቅ
አድርጎ እንዳገለገለ
እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ
በመዋደድ በቅንነት ኑሩ።
ጠላትም እንዳያጠቃችሁ
ትዕግሥት ይሙላባችሁ አሜን።
ጠላትም እንዳያጠቃችሁ
ትዕግሥት ይሙላባችሁ አሜን።
፫፡ በአሕዛብ ፊት ሞገስ ይስጣቸሁ
ፊቱን ያብራላችሁ።
ሰዎች ቅድስናችሁን አይተው
ጌታን እንዲያከብሩት
በተራራ ላይ የተሠራች ቤት
መደበቅ አይቻላትምና።
የአባታችሁ ስም እንዲጠራ
ብርሃናችሁ ይብራ አሜን።
የአባታችሁ ስም እንዲጠራ
ብርሃናችሁ ይብራ አሜን።
፬፡ የአብርሃም የሣራ ቤት ያርግላችሁ
ፍሬን ያብዛላችሁ።
ዘራችሁ እንደ ምድር ሠራዊት
ይብዛ እንደ ከዋክብት።
የምድርን ፍሬ ይባርክላችሁ
ጌታ በጸጋው ያበልጽጋችሁ።
ከሁሉም በላይ አምላካችሁ
ብር ወርቅ ይሁንላች አሜን።
ከሁሉም በላይ አምላካችሁ
ብር ወርቅ ይሁንላች አሜን።
