መዝሙር 205 አምላክ ሆይ ባርከው የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ አምላክ ሆይ ባርከው
የሙሽሮችን ኪዳን
በቅዱስ መንፈስህ
አጽና አንድነታቸውን።
በደስታ በኅዘን
ባንድነት ሲኖሩ
አንተን በማመስገን
በጸጋህ ይኑሩ።
፪፡ ባርካቸው በቃልህ
ቀድስ ጋብቻቸውን
በቅዱስ ረድኤትህ
ጠብቃቸው ሁለቱን።
ፍቅርን አብዛላቸው
ሞገስም ሁናቸው
ወደ ሰማይ መንግሥት
በእምነት ምራቸው።
