መዝሙር 204 ኢየሱስ አስታረቀን የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ኢየሱስ አስታረቀን
በመስቀሉ ላይ ሞተልን።
ለእኛ ሲል ቤዛ ሆኖ
ኃጢአታችንን ሠረየው።
ያ ቸር መድኃኒታችን
አነጻን ከኃጢአታችን።
፪፡ በደልህ የከበደህ
ኃጢአተኛ ቅረበው
በደልህን እግሩ ስር
ብትጥል፥ ያሳርፍሃል
የሱስ ይቀበልሃል
ከኃጢአት ያድንሃል።
፫፡ በደስታ ላመስግነው
በደሌን ስለ አራቀው።
ተኰንኜ ነበርኩኝ
አሁን በደሙ ነጻሁኝ።
አሁን የምዘምረው
ላዳነኝ ጌታዬ ነው።
