መዝሙር 203 በክፎች ምክር የማይሄድ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ በክፎች ምክር የማይሄድ
የማይገኝ በእርኩስ መንገድ።
ከኃጢአተኞች የራቀው
ጌታችን እርሱን ባረከው።
፪፡ በአምላክ ሕግ ደስ የሚለው
ቀን ሌትም የሚያስበው።
በልቡ የሚያደርገው
ጌታችን እርሱን ባረከው።
፫፡ በውኃ ዳር እንዳለች ዛፍ
ቅጠሏ እንደማይረግፍ
ከማበብና ከማፍራት
አያቋርጥም በየወራት።
፬፡ ኃጢአተኖች በፍርድ ቀን
ከጻድቃን ክፍል የላቸውም።
ጻድቃን ሕይወት ያገኛሉ
ኃጥአን ግን ይኰነናሉ።