መዝሙር 200 ሁሉም ዝግጁ ነው ጥሪውን ስማ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ሁሉም ዝግጁ ነው ጥሪውን ስማ፤
ወደ ቅዱስ ማዕድ ተጠርተሃል።
ጥሪውን አድምጠህ ወደ እራቱ ቅረብ፤
ሁሉም ለአንተ ነው አሁን ቅረብ።
፪፡ ወደ ሕይወት ወንዝ ና የተጠማህ፥
ሕይወትህን አድስ ከኃጢአትህ።
እልፍና አእላፋት ውኃውን ይጠጡታል፤
ዘላለም አይጐድልም ና የጠማህ።
፫፡ ወደ ጸጋ ዙፋን አሁን ቅረብ፤
በእምነት በትዕግሥት ሳትሰለች።
ኀዘንህን ሁሉ ደስታህንም ቢሆን፥
ወደ ጌታህ ቀርበህ አካፍለው።
፬፡ በዚች ዓለም ሥቃይ ሳትሸበር፥
ቶሎ ወደርሱ ና ሳትዘገይ።
ድሉና ምሕረቱ ሙላቱና ጸጋው
የዘለዓለም ነው ና አሁን ና።
፭፡ የሱስ አሳርፈን ከድካማችን፥
ኃጢአታችንን ደምስስልን።
ከጨለማ አውጣን ወዳንተ ሰብስበን፤
ሁላችን እንድናይ ብርሃንህን።