መዝሙር 2 አንመለስ ብለው አይሁድ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ እንመለስ ብለው አይሁድ
ሥራውን ቢቃወሙት፥
እንዲህ ብሎ ጮኸ የሱስ
የዓለሙ መድኃኒት።
ይህችን ዘማዊ ትውልድ፥
የአሁዶችንም ቤት፥
ከቶ በምን ይሆን እሷን
ምሳሌ የማደርጋት?
፪፡ በውነት እርሷም ትመስላለች
ዋዘኞች ሕፃናትን፥
በገበያ መሃል ቁመው፤
ዘፈን የሚዘፍኑት፤
በሜዳ ሰብስበው ያሉ
ጓደኞቻቸውን፤
እንደዚህም የሚሉትን፤
በዚያ የሚገኙትን።
፫፡ ቀናቀንላችሁ እኛ፥
አልዘፈናችሁም።
አስለቀስንላችሁ ደሞ፥
አላለቀሳችሁም።
ዮሐንስ መጥቶ ቢያስተምር፤
ሳይጠጣ ሳይበላ፤
ጋኔን አለው አሉት ደግሞ
እህልን የሚያስጠላ።
፬፡ እህል እየበላ እንደሰው፤
ቢያስተምር የሰው ልጅ፤
እነሆ ይሉት ጀመሩ
የቀራጭዎች ወዳጅ።
የሱስም እኒያን አገሮች፤
ነቀፋቸው አጥብቆ።
የሚበዛ ኃይልን አይተው፥
ነሰሐ ስላልገቡ።
