Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 198 የሕይወትን ምንጭ አየሁ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 198 የሕይወትን ምንጭ አየሁ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ የሕይወትን ምንጭ አየሁ
ሲወጣ ከጐኑ።
በየሱስ ደም የታጠቡ፥
ከኃጢአት ይነፃሉ።
፪፡ ያ ሕያው ምንጭ ያነፃኛል
ከሠራሁት በደል።
እቀበላለሁ በምሕረት፥
የኃጢአቴን ስርየት።
፫፡ ያንን ምንጭ ካየሁ በእምነት
እድናለሁ ከሞት።
አምላክ በፍቅሩ ብቻ ነው፥
ሰውን ሁሉ ያዳነው።
፬፡ በሰማያት አዲስ መዝሙር
ልዘምር ለርሱ ክብር።
ላነፃኝ በምሕረቱ፥
ላገባኝ በቤቱ።

Exit mobile version