Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 195 ኦ የሱስ ጌታዬ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 195 ኦ የሱስ ጌታዬ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ ኦ የሱስ ጌታዬ
አመሰግንሃለሁ።
ቅዱስ እራትህን
ሰጥተኸኛል አሁን።
በከበረ ደምህ
ነፍሴን ስላረካህ።
ሰላምና ደስታ
በእርሱ አገኘሁ።
፪፡ የኃጢአቴን ሸክም
ከኔ አስወገድህልኝ።
ዘላለማዊ ጽድቅ
ፍጹም አጎናጸፍኸኝ።
በጸጋህ የእምነት ኃይል
ካንተ ተቀበልሁ።
በጽኑ ሕማምህ
ዕረፍት አገኘሁ።
፫፡ ታዳጊ ጌታ ሆይ
እኔ ያንተ ገንዘብ ነኝ።
ከኃያሉ እጅህ
ከቶ ማንም አይነጥቀኝ።
በሕይወቴ ዘመን
ከአንተ እንዳልለይ።
በቅዱስ መንፈስህ
ዘወትር እርዳኝ አሜን።

Exit mobile version