መዝሙር 192 እንዴት ያለ ድንቅ ለውጥ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ እንዴት ያለ ድንቅ ለውጥ በሕይወቴ ሆነ
የሱስን ካገኘሁ ወዲህ፥
የፈለግሁት ብርሃን በነፍሴ ውስጥ አለ፥
የሱስን ካገኘሁ ወዲህ።
የሱስን ካገኘሁ ወዲህ፥
የሱስን ካገኘሁ ወዲህ፥
የደስታ ሙላት በልቤ ይጎርፋል፥
የሱስን ካገኘሁ ወዲህ።
፪፡ ከመኰብለልና ከጥፋት ድኛለሁ
የሱስን ካገኘሁ ወዲህ፥
ከብዶኝ ከነበረ ኃጢአት ነጻሁኝ፥
የሱስን ካገኘሁ ወዲህ።
የሱስን . . .።
፫፡ የተረጋገጠ ጽኑ ተስፋ አለኝ
የሱስን ካገኘሁ ወዲህ፥
የጥርጥር ጭጋግ በመንገዴ የለም፥
የሱስን ካገኘሁ ወዲህ።
የሱስን . . .።
፬፡ በሞት ሸለቆ ውስጥ ብርሃን በርቶልኛል
የሱስን ካገኘሁ ወዲህ፥
የሰማይን ቤት ደጅ ከሩቅ አየዋለሁ፥
የሱስን ካገኘሁ ወዲህ።
የሱስን . . .።
፭፡ እሄዳለሁ ልኖር በሰማይ ከተማ
የሱስን ካገኘሁ ወዲህ፥
በጣም ደስ ይለኛል ጉዞዬን ስቀጥል፥
የሱስን ካገኘሁ ወዲህ።
የሱስን . . .።
