Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 19 እነሆ ለሕዝብ ዛሬ የዘፈን ግጥሞች

መዝሙር 19 እነሆ ለሕዝብ ዛሬ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009

 

፩፡ እነሆ ለሕዝብ ዛሬ
መድኅን ተወለዶአል።
የምሥራቹ ወሬ
ወዳለም ደርሶአል።
ክርስቶስ መድኃኒታችን
መጥቶአል ለሁላችን
ቤዛችን እንዲሆን።
፪፡ አስቡ ምልክቱን
በጨርቅ ተጠቅልሎ
ታያላችሁ ሕፃኑን
በበረት ተኝቶ።
እርሱ ድንቅ መካር ኃያል
አምላካችን ይነግሣል
ብፅዕና ይሰጣል።
፫፡ የሰማይ ጭፍሮች ታዩ
አብረው ከመላኩ
አምላክን አከበሩ
እንደዚህ ዘመሩ
ክብር ላምላክ በአርያም
በምድር ይሁን ሰላም
ለሰውም በጎ ፈቃድ።

Exit mobile version