መዝሙር 189 ጌታ ሆይ ጩኸቴን ስማ የዘፈን ግጥሞች
Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus. vertsion 2009
፩፡ ጌታ ሆይ ጩኸቴን ስማ
ካልረዳኸኝ እጠፋለሁ።
ምሕረትህንም አምጣልኝ፥
እንዳለሁ ውሰደኝ።
እንዳለሁ ውሰደኝ
እንዳለሁ ውሰደኝ
ያንተ ሞት ነው ዋስትናዬ፥
እንዳለሁ ውሰደኝ።
፪፡ ተስፋ ቢስ በደለኛ ነኝ
ደምህን አፈሰሰክ ለኔ።
ተግባሬ በቂ አይደለም፥
እንዳለሁ ውሰደኝ።
እንዳለሁ . . .።
፫፡ ዝግጅት ላደርግ አልችልም
ቃሌን ከቶ አልጠብቅም።
ስለ ስምህ ብለህ ማረኝ፥
እንዳለሁ ውሰደኝ።
እንዳለሁ . . .።
፬፡ በእግርህ ሥር ተመልከተኝ
እንደ ፈቃድህ አድርገኝ።
ጀማሪና ፈጻሚ ነህ፥
እንዳለሁ ውሰደኝ።
እንዳለሁ . . .።
